የደንበኛ አገልግሎት በኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የእንግዳ አቀባበል፣ መስተንግዶ አሰጣጥ ታሪክ እና ባሕል እስከ ዛሬ ድረስ ለደንበኞች የአገልግሎት መጎልበት ጉልህ አስተዋጽዖ አበርክቷል። ሥነ ቃሎቻችን ከደንበኛ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ትክክለኛው ግንዛቤ እንዲኖረን አድርገዋል።
“ከፍትፍቱ ፊቱ፤ ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል።”
የደንበኛ አገልግሎት መመሪያ መጽሐፍ
ከልምድ ወደ ልኀቀት!
በእለት ተእለት የሰው ልጅ መስተጋብር የዳበረ የአገልግሎት አሰጣጥ ልምድ፣ እውቀት እና ልኅቀት



የሽፋን ምስሉ ፅንሰ ሀሳብ እና የደራሲው ልምድ
በእለት ተእለት የሰው ልጅ መስተጋብር የዳበረ የአገልግሎት አሰጣጥ ልምድ፣ እውቀት እና ልኅቀት
የመጽሐፉ ዋና ሀሳብ
"ደንበኞች የማንኛውም ሥራ መሠረት ናቸው። ግን ልብ የሚነካ አገልግሎት መስጠት ብቻ በቂ አይደለም - ሥርዓት፣ ሙያዊ ክህሎት፣ እና የአሠራር ጥልቅ ግንዛቤን ይጠይቃል።"
Yonas Negussie
ደንበኛሎጂን ይቃኙ
ከመጽሐፉ ጀርባ ያለው ልምድ
ከመጽሐፉ የተቀነጨቡ
የደንበኛሎጂን እይታ የሚያንጸባርቁ ሀሳቦች
የኢትዮጵያ የእንግዳ አቀባበል፣ መስተንግዶ አሰጣጥ ታሪክ እና ባሕል እስከ ዛሬ ድረስ ለደንበኞች የአገልግሎት መጎልበት ጉልህ አስተዋጽዖ አበርክቷል። ሥነ ቃሎቻችን ከደንበኛ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ትክክለኛው ግንዛቤ እንዲኖረን አድርገዋል።
“ከፍትፍቱ ፊቱ፤ ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል።”
እውነተኛ አገልግሎት ከስልጠና በላይ ነው። እርሱም ከውስጣችን የሚመነጭ የማገልገል ባህል ነው። አገልግሎት ማለት ሌላውን ማክበር፣ የሌላውን ጊዜ መውደድ እና የሌላውን ችግር እንደ ችግራችን መቁጠር ነው።
ስህተት መስራት የሰው ባህርይ ነው፤ ነገር ግን ስህተታችንን አምነን እንዴት እንደምናስተካክል ማቀድ ለሙያው ያለንን ክብር እና ጥረት ያሳያል። የአገልግሎት ማስተካከያ የእርምት እርምጃዎችን እንድንወስድ የሚመራ ንድፍ ነው።
ስሜታዊ ብስለት ደንበኛን ያስተናግዳል፤ አዕምሯዊ ብልህነት ደግሞ ችግሩን ይፈታዋል።
Yonas Negussie
የዮናስ ንጉሤ "ደንበኛሎጂ" መጽሐፍ፥ የኢትዮጵያን ባህላዊ የእንግዳ ተቀባይነት እሴቶች ከዘመናዊ የደንበኛ አገልግሎት መርሆች ጋር በማዋሃድ በኢትዮጵያ የንግድና አገልግሎት ዘርፍ ያለውን ክፍተት ለመሙላት የተፃፈ ወሳኝ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ደንበኛ አገልግሎትን እንደ ተቋማዊ ባህል እና የዘላቂ ስኬት መሰረት አድርጎ ይወስዳል።
በተለይም የውስጥ ደንበኛ (ሠራተኛ) እርካታ ለውጫዊ ደንበኛ አገልግሎት ያለውን ወሳኝ ድርሻ በሥነ-ልቦናዊ ዕይታ ይተነትናል። አሥራ አራት ምዕራፎችን የያዘው ይህ መጽሐፍ፤ የዲጂታል ዘመንን ተግዳሮቶች፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ተፅዕኖን እና ተግባራዊ የአገልግሎት ማስተካከያ ስልቶችን በዝርዝር ይዳስሳል።
በእያንዳንዱ ምዕራፍ መጨረሻ ላይ የተካተቱት ለውይይት የሚሆኑ መልመጃዎች፣ መጽሐፉን ለድርጅት መሪዎች፣ ለሥራ ፈጣሪዎችና ለባለሙያዎች ጥራት ያለው ተግባራዊ መመሪያ ያደርጉታል። በተጨማሪ፣ የትኛውም የኅብረተሰብ ክፍል ሊያነበው የሚገባ፣ እጅግ ጠቃሚ ሥራ ነው።
ዓለማየሁ ተክለ ማሪያም (ዶ/ር፤ ፕሮፌሰር) አ.አ.ዩ.